እኛ እዚህ አስፈላጊ ነን
የታኮማ ፓርክ ፍትሃዊነት እርምጃ
ጣቢያዎችን ከጎቦኙ እና እንቅስቃሴዎችን ካጠናቀቁ ቡኋላ ሀሳብዎን ለማካፈል የዳሰሳ ጥናታችንን ይሙሉ እና እኛ በምንኖርበት ነጻ እና ልዩ የሆነ- የታኮማ ፓርክ የእኩልነት የእግር ጉዞ ቲ-ሸርት ይውሰዱ! (ቲ-ሸርት ለመቀበል የአሜሪካ አድራሻ ማቅረብ አለብዎት).
አጠቃላይ
በማህበረሰባችን ውስጥ ፍትሃዊነት የበለጠ በአዲስ መልክ ለማወቅ እንኳን በደህና መጡ። የታኮማ ፓርክ ፍትሃዊነት እርምጃ የተዘጋጀው ማን እንደሆንን እንድንመረምር እና በሌላው ዘንድ ዋጋ ያለን እና እንደተካተትን ፍትሃዊነትን የበለጠ እንድናውቅ የተዘጋጀ ነው። ከሌሎች ጋር በማውራት በሌላው ዘንድ ዋጋ ያላቸው መሆናቸውን እና የመካተት ፍላጎቶቻውን እንማራለን እንዲሁም እናበረታታለን። የግለሰብ ዋጋ አጠቃላይ ሃሳብ ጠቃሚ ሆኖ በሚኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ ማእከላዊ ነው። እያንዳንዱ ጣቢያ አስደሳች፣ የሰውነት እንቅስቃሴ ያለበት ተሞክሮ ውስጥ በማሳተፍ ውይይትን ለመፍጠር ተያይዘው ያሉ ጥያቄዎችን ይጠቀማል። ስለራሳችን እና ስለሌሎች እንድንማር እና እንድንረዳ ተጨማሪ ግብአቶች አሉ። እኛ እዚህ አስፈላጊ ነን።
እንዴት መጀመር እንደሚችሉ
የእርስዎን የፍትሃዊነት እርምጃ እንዴት እንደሚጀምሩ እዚህ ጋር አለ። በካርታው ላይ ያለ እያንዳንዱ የፒን ምልክት ተግባር ያለበትን ጣቢያ ይወክላል። በየትኛውም ጣቢያ መጀመር ወይም ማቆም ይችላሉ። እንደፈለጉ የፍትሃዊነት እርምጃን መጎብኘት ይችላሉ። የበለጠ ለማወቅ እና ተጨማሪ ግብአቶችን ለማግኘት እዚህ ጋር ጠቅ ያድርጉ። በታኮማ ፓርክ ማህበረሰብ ማእከል ውስጥ አስር ጣቢያዎች ሲኖሩ በአን መንገድ በቦላቫርድ ዩኒቨርስቲ አጠገብ ደግሞ ሰባት ጣቢያዎች አሉ።
“ትክክለኛ ለውጥ፣ ቀጣይነት ያለው ለውጥ የሚመጣው በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ በመውሰድ ነው።” ሩት ባድር ጊንስበርግ
የማህበረሰብ ጎዳና ጣቢያዎች
የTakoma ፓርክ ማህበረሰብ ማእከል መገኛ ቦታዎች (ፊላደልፊያ ጎዳና፣ ሆሊ ጎዳና እና ግራንት ጎዳና)
እርምጃዎችን መውሰድ
በማህበረሰቤ ማእከል የቅርጫት ኳስ መጫወቻ
ከአንድ ድንጋይ ወደ ሌላ ድንጋይ ይሂዱ። ትልቅ ድንጋዮች ላይ ብቻ ይርገጡ፣ ትንሽ ድንጋዮችን ብቻ ይርገጡ። ቀለም ይምረጡ እና ያን ቀለም ላይ ብቻ ይርገጡ።
ስኬታማ ስሜት እንዲሰማዎ የሚያደርገው ምንድነው? ኩሩስሜት እንዲሰማዎ የሚያደርገው ምንድነው? ግቦችዎ ምንድናቸው? ትልቅ እርምጃ መውሰድን ትናንሽ እርምጃ ከመውሰድ ጋር ያለውን ልዩነት ያስቡ። ራስዎን ለተግዳሮት ማዘጋጀት ምን አይነት ስሜት አለው?
“ትልቅ እና ፋይዳ ያለው ስራ መስራት እፈልጋለሁ፤ ነገር ግን ትናንሽ ስራዎችን ትልቅ እና ፋይዳ እንዳላቸው አድርጌ መስራት ዋና ስራዬ ነው።” ሄለን ኬለር
በብሎችን ማፈንዳት
በታኮማ ፓርክ ቤተ መጻህፍት መግቢያ
በብሎችን እየረገጡ ማግለሎችን ያፈንዱ እና ማረጋገጫዎችን ይናገሩ፡ የጥቁሮች ነፍስ ዋጋ አለው፣ የሴት ሃይል፣ እኔ አስፈላጊ ነኝ፣ እናንተ አስፈላጊ ናችሁ፣ እኛ አስፈላጊ ነን የሚሉትን ቃሎች ይቀዳዱ። በብሎቹን ሲያፈነዱ የራስዎን ንግግሮች ይበሉ።
የተሳሳተ አመለካከት ምንድነው? ግምት ምንደነው? ወገንተኝነት ምንድነው? ጭፍን ጥላቻ ምንድነው? ማግለል ምንድነው? ማረጋገጫ ምንድነው?
“ሁሉንም የምንጋፈጠውን ነገር መለወጥ አንችልም፣ ነገር ግን ሳንጋፈጥ ምንም ነገር መለወጥ አንችልም።” ጀምስ ባልድዊን
እርምጃውን መራመድ
የ Philadelphia Ave 200 ብሎክ
የድብ፣ የዝሆን የእንቁራሪት እርምጃዎችን ይከተሉ።
እንስሳ ቢሆኑ፣ ምን እንስሳ ይሆኑ ነበር? የሚወዱት እንስሳ ምንድነው እና ለምን? እንስሳቶች አብረው ለመኖር ምን ምን የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀማሉ? ሰዎች አብረው ለመኖር ምን ምን የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀማሉ? ልዩ እንደሆኑ የሚሰማዎ በምንድነው? ዋጋ ያለው እንደሆኑ የሚሰማዎ በምንድነው?
“ሁልጊዜ መደበኛ ለመሆን የሚጥሩ ከሆነ እንዴት አስደናቂ መሆን እንደሚችሉ መቼም አያውቁም።” ማያ አንጄሎ
በፍጥነት መሄድ
የ Philadelphia Ave እና Holly Ave ማእዘን
ከአንድ ሎግ ወደ ሌላ ሎግ ይዝለሉ።
አስጊ እርምጃ መውሰድ ምን ማለት ነው? አስጊ እርምጃ መውሰድ ምን አይነት ስሜት አለው? ጥሩ አስጊ እርምጃ መውሰድ ምሳሌ ይስጡ? መጥፎ ወይም አደገኛ አስጊ እርምጃ ምሳሌ ይስጡ?
"ሁል ጊዜ ብርሃን አለ፣ ደፍረን ለማየት ከቻልን ብቻ፡፡ እኛ ብቻ ለመሆን ደፋር ከሆንን።" አማንዳ ጎርማን
ሆፕ ፣ መዝለል እና መዝለል
Holly Ave ከ Hodges Ln ፊትለፊት
ድንጋይ ወይም ሳር ይፈልጉ። ወደ ቁጥር 1 ይወርውሩት። አንድ ቁጥርን ይዝለሉ እና ቁጥሮቹ ላይ እየረገጡ ይዝለሉ። ወደኋላ ይመለሱ እና ወደ ቁጥር 1 ተመልሰው መጥተው ድንጋዮን ያንሱ። አሁን ወደ ቁጥር 2 ይወርውሩት እና ይቀጥሉ። ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ተራ በተራ በመሆን መጫወት ይችላሉ።
ምን ምን ጨዋታዎችን ይወዳሉ? በቡድን ነው ወይስ ብቻዎን መጫወት የሚወዱት? ተራ በተራ ነገሮችን ማድረግ ምን ማለት ነው? ፍትሃዊ ማለት ምን ማለት ነው? ፍትሃዊ የሚለው ከእኩል ጋር ተመሳሳይ ነው?
“ፍትሃዊነት ሁሉም ተመሳሳይ ይቀበላሉ ማለት አይደለም። ፍትሃዊነት ማለት እያንዳንዱ ሰው የሚፈልገውን ያገኛል ማለት ነው።” ሪክ ሪኦርዳን
በጣትዎ መራመድ
Holly Ave እና Grant Ave ማእዘን
በጣትዎ በመቆም የእባቡን ሰውነት ከጭንቅላቱ እስከ ጭራው ይከተሉ።
በሆነ ጉዳይ ዙሪያ መሽከርከር ማለት ምን ማለት ነው? በሆነ ጉዳይ ላይ መናገር ሲችሉ ጸጥ ብለው ያውቃሉ? እንዲናገሩ የሚያደርግዎ ነገር ምንድነው?
“የድምጻችንን ጥቅም የምናውቀው ጸጥ እንድንል ስንደረግ ነው።” ማላላ ዩሳፍዛይ
ሚዛንን ጠብቆ መቆም
የ Grant Ave 300 ብሎክ
በገመዱ ላይ ሚዛንዎን ጠብቀው ይቁሙ፣ እግርዎትን ከፊት እና ከኋላ በማድረግ ይሂዱ። አየር ላይ እንዳሉ አስመስለወው ይቁሙ። ላለወቅደቅ ይሞክሩ።
በህይወትዎ ላይ ሚዛናዊነትን መያዝ ማለት ምን ማለት ነው? እንዲጨነቁ ወይም “ሚዛናዊ እንዳይሆኑ” የሚያደርግዎ ምንደነው? ቢወድቁስ? እንደገና መነሳት ይችላሉ?
“ጾታን እንደ ሁለት ተቃራኒ ወገኖች ከማየት ወጥተን እንደ ህብረቀለም ማየት መጀመር ያለብን ሰአት ነው።” ኢማ ዋትሰን
መምራት እና መከተል
On Grant Ave ከ Takoma Park መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ
ሌላኛው ሰው ፊት ለፊት ይቁሙ። አንደኛው ሰው መሪ ነው፤ ሌላኛው ይከተላል። ይደንሱ፣ አስቂኝ ፊቶችን ያሳዩ፣ እጅዎትን እና እግርዎን ያንቀሳቅሱ፣ ፈጣሪ ይሁኑ። በሌላ ቋንቋ ወይም በምልክት ቋንቋ የሆነ ነገር ይናገሩ። መሪውን እና ተከታዩን ያቀያይሩ።
በምን በምን እንመሳሰላለን፣ በምን በምን እንለያያለን? ከሌላው መለየት ምን አይነት ስሜት አለው? ኩሩስሜት እንዲሰማዎ የሚያደርገው ምንድነው? ልዩ እንደሆኑ የሚሰማዎ በምንድነው? መሪ ኖት ወይስ ተከታይ ኖት?
“ሌላው ሁሉም ሰው ስለተወሰደ ራስዎን ይሁኑ።” ኦስካር ዊልዴ
ንግግርዎን መራመድ
የ Grant Ave 300 ብሎክ
ከተረከዝ እስከ ጣት ድረስ የእግር አሻራውን ይከተሉ።
በእያንዳንዱ ቃል መካከል ይቁሙ። ትርጉሙ ምን እንደሆነ ያስቡ። እያንዳንዱ ቃል በቤተሰብዎ፣ በማህበረሰብዎ እና በሃገርዎ ያለውን ትርጉም ይናገሩ። እነዚህን እና የእርስዎን ማረጋገጫዎች ይናገሩ። እኔ ደግ ነኝ። እኔ ለማወቅ ጉጉ ነኝ። እኔ ፈጣሪ ነኝ። እኔ አስፈላጊ ነኝ።
“በሌላው ሰው ጫማ ውስጥ መሄድ” ማለት ምን ማለት ነው?
ደግ ኖት? ለማወቅ ጉጉ ኖት? ፈጣሪ ኖት? ሌሎችን ያከብራሉ? ራስዎን ያከብራሉ? እንደ ተካተቱ እንዲሰማዎ የሚያደርገው ምንድነው? ማረጋገጫ ምንድነው? እነዚህን እና የእርስዎን ማረጋገጫዎች ይናገሩ። እኔ ደግ ነኝ። እኔ ለማወቅ ጉጉ ነኝ። እኔ ፈጣሪ ነኝ። እኔ አስፈላጊ ነኝ።
“ሁሉም ትክክለኛ ትላልቅ አስተሳሰቦች የተወለዱት በእርምጃ መካከል ነው።” ፍሬድሪች ኒዜች
ትሪ ፖዝ
በታኮማ ፒኒ ቅርንጫፍ ፓርክ መግቢያ
እጆችዎን ጎንዎ ላይ በማድረግ በመቆም ይጀምሩ።
የሰውነትዎን ክብደት ወደ ግራ እግርዎ ያዘንብሉ። ቀኝ እግርዎን ምስሉ ላይ እንደሚታየው ያድርጉ።
እግርዎን በጉልበትዎ አስደግፈው አያስቀምጡ፣ ወይ በላዩ ወይም በታቹ ያድርጉ።
እጅዎን ከራስዎ በላይ ሲያደርጉ ወደውስጥ ይተንፍሱ፣ የእጅዎን ጣቶች ወደሰማይ ይዘርጉ። እርስ በእርስ ለመተያየት የውስጥ ጣቶችዎን ወደ ውስጥ ያዙሩ።
ለእርስዎ ከባድ የሆነ ነገር ምንድነው? ቀላል የሆነ ነገር ምንድነው? ልምምድ የሚጠቅመው ለምንድነው? የተረጋጉ ስሜት እንዲሰማዎ የሚያደርገው ምንድነው?
"ውድቀት አንድን ነገር በድጋሚ ለመጀመር ተጨማሪ እድሉ ብቻ ነው፣ በዚህን ጊዜ የበለጠ በብልህነት።" ሄነሪ ፎርድ
የአን ጎዳና ጣቢያዎች
የአን ጎዳና መገኛ ቦታዎች በከነዊክ ጎዳና እና ቦውልቫርድ ዩኒቨርሲቲ መሃል ነው
ትሪ ፖዝ
እጆችዎን ጎንዎ ላይ በማድረግ በመቆም ይጀምሩ።
የሰውነትዎን ክብደት ወደ ግራ እግርዎ ያዘንብሉ። ቀኝ እግርዎን ምስሉ ላይ እንደሚታየው ያድርጉ።
እግርዎን በጉልበትዎ አስደግፈው አያስቀምጡ፣ ወይ በላዩ ወይም በታቹ ያድርጉ።
እጅዎን ከራስዎ በላይ ሲያደርጉ ወደውስጥ ይተንፍሱ፣ የእጅዎን ጣቶች ወደሰማይ ይዘርጉ። እርስ በእርስ ለመተያየት የውስጥ ጣቶችዎን ወደ ውስጥ ያዙሩ።
ለእርስዎ ከባድ የሆነ ነገር ምንድነው? ቀላል የሆነ ነገር ምንድነው? ልምምድ የሚጠቅመው ለምንድነው? የተረጋጉ ስሜት እንዲሰማዎ የሚያደርገው ምንድነው?
“አስተሳሰብዎን ይቀይሩ እና አለምዎን ይቀይሩ።” ኖርማን ፒሊ
በጣትዎ መራመድ
በጣትዎ በመቆም የእባቡን ሰውነት ከጭንቅላቱ እስከ ጭራው ይከተሉ።
በሆነ ጉዳይ ዙሪያ መሽከርከር ማለት ምን ማለት ነው? በሆነ ጉዳይ ላይ መናገር ሲችሉ ጸጥ ብለው ያውቃሉ? እንዲናገሩ የሚያደርግዎ ነገር ምንድነው?
“በጣቶችዎ የሚራመዱ ከሆነ ረጅም ጊዜ የሚቆይ አሻራ ጥለው ማለፍ አይችሉም።” ማሪዮን ብላኪይ
ንግግርዎን መራመድ
በእያንዳንዱ ቃል መካከል ይቁሙ። ትርጉሙ ምን እንደሆነ ያስቡ። እያንዳንዱ ቃል በቤተሰብዎ፣ በማህበረሰብዎ እና በሃገርዎ ያለውን ትርጉም ይናገሩ። እነዚህን እና የእርስዎን ማረጋገጫዎች ይናገሩ። እኔ ደግ ነኝ። እኔ ለማወቅ ጉጉ ነኝ። እኔ ፈጣሪ ነኝ። እኔ አስፈላጊ ነኝ።
ደግ ኖት? ለማወቅ ጉጉ ኖት? ፈጣሪ ኖት? ሌሎችን ያከብራሉ? ራስዎን ያከብራሉ? እንደ ተካተቱ እንዲሰማዎ የሚያደርገው ምንድነው? ማረጋገጫ ምንድነው? እነዚህን እና የእርስዎን ማረጋገጫዎች ይናገሩ። እኔ ደግ ነኝ። እኔ ለማወቅ ጉጉ ነኝ። እኔ ፈጣሪ ነኝ። እኔ አስፈላጊ ነኝ።
“የድምጻችንን ጥቅም የምናውቀው ጸጥ እንድንል ስንደረግ ነው።” ማላላ ዩሳፍዛይ
ሆፕ ፣ መዝለል እና መዝለል
ድንጋይ ወይም ሳር ይፈልጉ። ወደ ቁጥር 1 ይወርውሩት። አንድ ቁጥርን ይዝለሉ እና ቁጥሮቹ ላይ እየረገጡ ይዝለሉ። ወደኋላ ይመለሱ እና ወደ ቁጥር 1 ተመልሰው መጥተው ድንጋዮን ያንሱ። አሁን ወደ ቁጥር 2 ይወርውሩት እና ይቀጥሉ። ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ተራ በተራ በመሆን መጫወት ይችላሉ።
ምን ምን ጨዋታዎችን ይወዳሉ? በቡድን ነው ወይስ ብቻዎን መጫወት የሚወዱት? ተራ በተራ ነገሮችን ማድረግ ምን ማለት ነው? ፍትሃዊ ማለት ምን ማለት ነው? ፍትሃዊ የሚለው ከእኩል ጋር ተመሳሳይ ነው?
“ፍትሃዊነት ሁሉም ተመሳሳይ ይቀበላሉ ማለት አይደለም። ፍትሃዊነት ማለት እያንዳንዱ ሰው የሚፈልገውን ያገኛል ማለት ነው።” ሪክ ሪኦርዳን
በፍጥነት መሄድ
ከአንድ ሎግ ወደ ሌላ ሎግ ይዝለሉ።
አስጊ እርምጃ መውሰድ ምን ማለት ነው? አስጊ እርምጃ መውሰድ ምን አይነት ስሜት አለው? ጥሩ አስጊ እርምጃ መውሰድ ምሳሌ ይስጡ? መጥፎ ወይም አደገኛ አስጊ እርምጃ ምሳሌ ይስጡ?
“ሁልጊዜ መደበኛ ለመሆን የሚጥሩ ከሆነ እንዴት አስደናቂ መሆን እንደሚችሉ መቼም አያውቁም።” ማያ አንጄሎ
በብሎችን ማፈንዳት
በብሎችን እየረገጡ ማግለሎችን ያፈንዱ እና ማረጋገጫዎችን ይናገሩ፡ የጥቁሮች ነፍስ ዋጋ አለው፣ የሴት ሃይል፣ እኔ አስፈላጊ ነኝ፣ እናንተ አስፈላጊ ናችሁ፣ እኛ አስፈላጊ ነን የሚሉትን ቃሎች ይቀዳዱ። በብሎቹን ሲያፈነዱ የራስዎን ንግግሮች ይበሉ።
የተሳሳተ አመለካከት ምንድነው? ግምት ምንደነው? ወገንተኝነት ምንድነው? ጭፍን ጥላቻ ምንድነው? ማግለል ምንድነው? ማረጋገጫ ምንድነው?
“ጾታ ላይ ያለው ችግር ማንነታችን እንድናውቅ እንደማድረግ ምን መሆን እንዳለብን እለሚያዘን ነው።” ችማማንዳ ጎዚ አዲቺ